1ይ ቆሮንቶስ 2:1-2 - :ኣሕዋተየ፡ ኣነ ድማ ኣብ ማእከልኩም ከሎኹ፡ ብዘይ የሱስ ክርስቶስ፡ ንሱ ኸኣ እቲ እተሰቕለ፡ ሓደ ነገር እኳ ኸም ዘይ

በ ስም ኣብ ወወልድ ወ መንፈስ ቅዱስ ኣሃዱ ኣምላክ ኣሜን።

Friday 11 May 2012

ሰበር ዜና መጋቤ ሀዲስ በጋሻው ደሳለኝና አባ ሠረቀ ብርሃን ወ/ሳሙኤል ከተከከሰሱበት የኑፋቄ ክስ ነፃ ወጡ!!


ሰበር ዜና መጋቤ ሀዲስ በጋሻው ደሳለኝና አባ ሠረቀ ብርሃን ወ/ሳሙኤል ከተከከሰሱበት የኑፋቄ ክስ ነፃ ወጡ!!


ውሳኔው በማኅበረ ቅዱሳን ላይ መንፈሳዊና ሞራላዊ ክስረት የሚያደርስ ሲሆን በዓለም ዙሪያ ላሉ የቤተክርስቲያናችን ቤተሰቦች ታላቅ ብሥራት ነው
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባዔ ትላንት ሐሙስ ግንቦት 2 ቀን 2004 ዓ.ም ቀጥሎ በዋለው ስብሰባ መጋቤ ሀዲስ በጋሻው ደሳለኝንና አባ ሠረቀ ወ/ሳሙኤልን ከተከሰሱበት "የፕሮቴስታንታዊ ተሀድሶ ኑፋቄ" ክስ ነፃ ያወጣቸው መሆኑን የደረሰን መረጃ አመለከተ፡፡
"ማኅበረ ቅዱሳን" በተለይ በሁለቱ የቤተክርስቲያን ልጆች ላይ ያስነሳው ሁከትና የክስ ድሪቶ በሥጋዊ ዓይን ሲታይ እጅግ በጣም ታላቅ ነበር፡፡ መጋቤ ሀዲስ በጋሻው ከተሰጠው የስብከት ፀጋ በተጨማሪ ማቆች አደብ እንዲገዙ በሚሰጣቸው ምክር በመበሳጨት እንዲሁም አባሠረቀ ብርሃን የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ኃላፊ በነበሩበት ወቅት ሕግና ሥርዓትን ጠብቆ እንዲይዝ፣ እዚህም እዚያም እየዘለለ እንዳያውክና መዋቅሩን ጠብቆ እንዲሠራ፣ እንዲሁም ስሕተቶቹን እንዲያርም አግባብ ባለው መንገድ ስለያዙት በሁለቱ አገልጋዮች ላይ ያወረደው ውርጅብኝ በምዕመናን ዘንድ አካላዊና ሥነ ልቦናዊ እንዲሁም መንፈሳዊ ጫናን ያሳደረ ነበር፡፡
በመጋቤ ሀዲስ በጋሻው ደሳለኝና እና በአባ ሠረቀ ብርሃን ወ/ሳሙኤል ላይ የቀረበው የሐሰት ክስ ድሪቶ ሊገፈፍ የቻለው በአገልግሎት ዘመኖቻቸው የፈጸሟቸው የጽሑፍ፣ የምስልና የድምፅ አስተምህሮቻቸው ተፈትሾ ሕጸጽ ባለመገኘቱ መሆኑ ታውቋል፡፡ ይህ በሊቃውንት ጉባዔ የተመረመረው የአስተምህሮዎቻቸው ውጤት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባዔ ከመረመረውና ከተወያየበት በኋላ ያለ ምንም ልዩነት በሙሉ ድምፅ አጽድቆታል፡፡
ወትሮም ቢሆን "ማኅበረ ቅዱሳን" ከንቱ ጩኸትና ልፍለፋ ካልሆነ በስተቀር አንዳች ተጨባጭ እውነት ያዘለ ቁም ነገር እንደሌለው ይታወቃል፡፡ ቤተክርስቲያን የሰዎች ስብስብ እንደመሆኗ መጠን ከሰዎች የአገልግሎት ስሕተት ነፃ ናት ልትባል አትችልም፡፡ ሆኖም እነዚህ ስሕተቶች ትልቅም ይሁኑ ትንሽ የሚታረሙበት አግባብ አላቸው፡፡ በተለይም በቀኖና ቤተክርስቲያንና በፍትሐ ነገሥቱ አገልጋዮችና ምዕመናን እንደየደረጃቸው ስሕተት ሲፈጽሙ የሚታረሙበትና ከእናት ቤተክርስቲያን ጋር ታርቀው ስለሚሄዱበት ሁኔታ በግልጽ ተቀምጧል፡፡ ነገር ግን ማኅበረ ቅዱሳን ራሱን ከቀኖና ቤተክርስቲያን፣ ከፍትሐ ነገሥት፣ ከጠቅላይ ቤተክህነት፣ ከሊቃውንት ጉባዔና ከሲኖዶስ በላይ በማስቀመጥ፣ ከሳሽና ፈራጅ በመሆን በቤተክርስቲያን ላይ ከፍተኛ ቀውስ አስከትሏል፡፡
ለዓመታት በዘለቀው በዚህ ቀውስ የተዘጉ ቤተመቅደሶች፣ የተሰደዱ ምዕመናንና አገልጋዮች፣ የደረሰ ድብደባ፣ እንግልት፣ እሥራትና ሞት፣ በዚህ ሁኔታ ድንግርግር ውስጥ ገብተው የዕምነት እሴታቸው የተሸረሸረባቸው ስንቶች እንደሆኑ ቤቱ ይቁጠረው፡፡ በተለይም የዋሃን ተከታዮቹ መሪዎቻቸው የደገሱትን ሳያውቁ በዘረጉት የሁከት ፕሮጀክት በደመነፍስ በመሳተፍ ስንቱን ወንድሞቻቸውንና እህቶቻቸውን እንደበደሉ እና የቤተክርስቲያንን የአምልኮ ሥርዓት እንዳወኩ ማስተዋል ይቻላል፡፡
ማኅበረ ቅዱሳን ደጋግመን እንደምንለው ፖለቲካዊ የማፊያ ድርጅት እንጂ ሃይማኖታዊ አይደለም፡፡ የአባላት ቁጥሩና ዝርዝር በቤተክርስቲያንና በመንግሥት አይታወቅም፤ የሀብትና የገንዘብ ምንጩ በትክክል አይታወቅም፣ የወጪውና የገቢው  አርዕስት አይመዘገብም፤ ሀብትና ንብረቱና የፋይናንስ እንቅስቃሴው ኦዲት ተደርጎ አይታወቅም፡፡ ኦዲት ለማሰደረግም ከቤተክርስቲያን አቅም በላይ ሆኗል፡፡
በዚህ የጨለማ ዓለም እንቅስቃሴው ሲዳክር በዝቋላ ገዳምና በዋልድባ ገዳም ሳቢያ ፖለቲካዊ ማንነቱ በይበልጥ የተጋለጠው "ማኅበረ ቅዱሳን" ኪሣራ ያጋጠመው ሲሆን አሁንም ባልተሰጠው ሥልጣን "የፕሮቴሰታንታዊ ተሀድሶ" አታሞውን ሲደልቅ የከረመበት የዓመታት ልፋቱ እንደጉም ተንኖበት መንፈሳዊ ኪሣራ ውስጥም ለመዘፈቅ ተገዷል፡፡
የመጋቤ ሀዲስ በጋሻው ደሳለኝና የአባ ሠረቀ ብርሃን ወ/ሳሙኤል ነፃነት በቅን አማንያን ዘንድ ቀድሞም የሚታወቅ ቢሆንም፣ በተለይ በተቀነባበረና በፈጠራ የሐሰት ክስ የተከመረባቸው የጎደፈ ስም እንደዚህ ጥርት ባለና በተረጋጋ ሁኔታ መወሰንና መንጻት መቻሉ አስደሳች ነው፡፡ መቶ በጎች ያሉት ሰው አንዲት በግ ብትጠፋበትና መልሶ ቢያገኛት ካልጠፉት ከዘጠና ዘጠኙ በጎች ይልቅ ጠፍታ በተገኘችው በግ ደስ እንደሚለው፣ የእነዚህ ሁለት አገልጋዮች እንደ ጠላት ሃሣብ ሳይሆን በበረቱ መቆየት ለሁላችንም ብሥራት ነው፡፡
እግዚአብሔር በምሕረቱና በቸርነቱ ይጠብቀን!!!
አሜን!!!

2 comments:

  1. Ha ha shame on you! I repeat it again shame on you ! Don't try to touch Mahibere kidusan...untouchable ......don't waste your time..

    ReplyDelete
  2. mahbere kidusan the evl of the baible

    ReplyDelete