ማኅበረ ቅዱሳን አቡነ ጳውሎስን ከሥልጣን ለማውረድ ታጥቆ ተነስቷል
- በጠቅላይ ቤተ ክህነት ሰራተኞች ስም ደብዳቤም አሰራጭቷል
ሰሞኑን እየገጠመው ካለው ችግርና
ፓትርያርኩም በውሳኔዎች ላይ ቆራጥ እየሆኑ በመምጣታቸው የእሳቸው ስልጣን ላይ መቆየት ለህልውናዬ ያሰጋኛል ብሎ በማሰቡ ማኅበረ
ቅዱሳን እሳቸውንን የማውረድ ዘመቻ ውስጥ ውስጡን ጀምሯል፡፡ በተለይም በጠ/ቤተ ክህነቱ ሠራተኞች ስም “የዳኛ ያለህ! ለቤተ
ክርስቲያኒቱ ዳኝነት ይታይላት” በሚል ርዕስ ያሰራጨው ጽሑፍ ለቅዱስ ሲኖዶስ አባላት የደረሰ ሲሆን ይህንኑ እንደ ግብአት
ተጠቅመው አጀንዳ ለማስያዝና ቅዱስነታቸውንን የማውረድ ሴራ እንዲሸርቡ የተመከሩ ጳጳሳት እንዳሉ ይነገራል፡፡
ምንም እንኳ የጽሁፉ ምንጭ
የጠቅላይ ቤተ ክህነት ሰራተኞች ናቸው ቢባልም ጹሁፉ ግን ከማኅበረ ቅዱሳን እንደወጣ እና አብዛኛው የጠ/ቤተ ክህነት ሠራተኞችችም
ጽሁፉ መጻፉን እንኳን እንደማያውቁ ለመረዳት ተችሏል፡፡ ከዚህ በጠ/ቤተ ክህነቱ ሠራተኞች ስም ካሰራጨው ጽሁፍ በተጨማሪ
በቆዩትና አዳዲስ እየከፈታቸው ባሉ ብሎጎች ሀሳቡን እያንሸራሸረ የሚገኝ ሲሆን ይህም የታቀደው ተሳክቶ ፓትርያርኩ ቢነሱ ሕዝቡ
ግር እንዳይለው ግንዛቤ መፍጠሪያ መንገድ መሆኑም ታውቋል፡፡
በአንዳንድ ብሎጎችም ቅዱስነታቸውን “እናሸንፋቸውና ቤ/ክ/ ሰላም ታግኝ” በማለት ይፋ የስልጣን ማፈናቀል ዘመቻ ከፍተዋል፡፡ ብሎጎቹ በጠቅላይ ቤተ ክህነት ሰራተኞች ስም ከተጻፋ
ደብዳቤ ጋር በይዘትም በቅርጽም ተመሳሳይ የሆነ ጽሁፍ የለቀቁ ሲሆን ልዩነቱ ብሎጎቹ ላይ ያለው ጽሁፍ በግል አስተያየት ስም
የተጻፉ መሆናቸው ነው፡፡
http://www.awdemihret.blogspot.com/2012/05/blog-post_3442.html
No comments:
Post a Comment